አኬልዳማ፤ የደደቢት ደደቦች ድራማ
ዛሬ በዚህ ጽሁፌ የማነሳው ጉዳይ ወያኔ ሰሞኑን አኬልዳማ በሚል ርእስ የነዛውን የውሸት ድራማ
በተመለከት አንድ ነገር ለማለት ነው። በመጀመሪያ ደረጃ የኢትዮጵያ ህዝብ አይደለም ዛሬ የአለም
ህዝብ ወያኔ ማለት ውሸት፤ ሌብነት፤ ክህደት ማለት መሆኑን በመረዳቱ፤ ይህ እየተነዛ ያለው
ፕሮፓጋንዳ ማንንም የኢትዮጵያን ህዝብ ያሳምናል ብየ አላምንም።
ቀደም ሲል ባሳለፍናቸው ሀያ ዓመታት እንደተማርነው፤ በወያኔ የፈጠራ ወሬ፤ በወያኔ የቴሌቪዥን
ፕሮፓጋንዳ ድራማ ውስጥ የሚሳተፉት ተዋንያን የሚመለመሉት በሶስት አይነት ሁኔታ ነው።
1
ኛ. እራሳቸው የወያኔ ወይም የተለጣፊ ድርጅቶቻቸው አባላት የሆኑ
2
ኛ. ለየት ላለ ተልኮ ወይም ለየት ያለ የመተወን ችሎታ ያላቸውና ተከፍሏቸው ለመስራት
ፍቃደኛ የሆኑ
3
ኛ. በማሰቃየት፤ የሚፈለገውን ነገር እንዲናገሩ የሚደረጉ በእስር ላይ የሚገኙ ግለሰቦች ናቸው።
ይህንን በሀያ አመታት ጉዞአችን ተምረናል።
የወያኔዎችን አስተሳሰብ ኢቮሉሽንም ሪቮሉሽንም ሊለውጠው ያልቻለ እጅግ ያይምሮ ዝግመት
ያለባቸው ሰዎች መሆናቸውን እራሳቸው የሚገልጹበት ሁኔታ በተለያዩ አጋጣሚዎች ይከሰታል።
ካጋጣሚዎቹ አንዱ የሰሞኑ አኬልዳማ ነው።
“ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል” የሚለው
መርሀቸው ገና ጫካ እያሉ በየቀኑ ሀያ ሺህ ፤ አስር ሺህ የደርግ ወታደር ገደልን አያሉ ፍጹም
ውሸት ይነዙ እንደነበረ ፤ መንግስት ነን ካሉ በሗላም ያው በሽታቸው አለቃችሁ ብሏቸው፤
ያለፉትን ሀያ ዓመታትም ፍጹም ውሸት ብቻ በማውራት ጉዞውን ቀጥለዋል።
የሀገሪቱን የቁርጥ ቀን ልጆች አሸባሪዎች እያሉ በቴሌቭዢን ድራማ የሚወነጅሉት የወያኔ
ደናቁርት፤ በአዲስ አበባ ባለፉት ሀያ ዓመታት በተለያዩ ጊዜያት ፈንጂ እያፈነዱ፤ ተኩስ እየከፈቱ
ንጹሀን ዜጎችን እየገደሉ ሌሎች ላይ ሲያላክኩ መኖራቸውን የአሜሪካ ኢምባሲ ለሀገሩ መንግስት
በሚስጥር ያስተላልፍ የነበረውን ሪፖርት፤ ዊኪሊክ ባዝረከረከው ሚስጢር አስረድቶን ነበር።
የሽብርተኛ ትክክለኛ ትርጉሙ ያነው። ትክክለኛው አሸባሪም ወያኔ ነው።
የቀድሞውን መምህራን ማህበር በማፍረሱ ትግል ላይ ወያኔ የዶክተር ታዬን ድራማ ሲሰራ፤ በሀይል
መንግስት ለመገልበጥ ነው ብሎ ጥቂት ጠመንጃ ለብቻ፤ ዶክተር ታዬንና አባሪዎቹን ለብቻ ፊልም
አንስቶ በቴሌቪዥን እየቀጣጠለ ህዝቡን ያናድድ የነበረ ዘመን፤ የዶክተር ታዬ አባሪ ነው ተብሎ
ከታሰረው ሰው ጋር የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ በአዲስ አበባ ወህኒ ቤት አብሮ የመታሰር እድል አግኝቶ
ነበር። ለአንድ ዓመት ያህል። እንደ ሀገር አቆጣጠር
1989። በወቅቱ ከግለሰቡ ጋር ጥሩ ቀረቤታ
ስለነበረኝ ብዙ ብዙ ነገሮችን አንስተን እንጫወት ነበር። የዶክተር ታዬ አባሪ ተብሎ የታሰረው
ሰው እንኳን ዶክተር ታዬን ሊያውቀው ስሙንም ሰምቶ የማውቅ፤ ከሀገር ሀገር እየተዘዋወረ
በመነገድ ኑሮውን የሚመራ፤ ተራ ዜጋ ነበር። ሲያዝም ይህነው ብሎ በማያውቀው ምክንያት ዲላ
ከተማ የለት ተለት ተግባሩን በማከናወን ላይ እንዳለ ነበር። ከዚያ በሗላ አዲስ አበባ ተወስዶ
ሰውየው የዶክተር ታዬ አባሪ እንዲሆን የተከተለውን ስቃይ አንባቢያን ይገምቱ። የኢትዮጵያን
ህዝብ ባያሳምንም ምናልባት አንዳንድ የውጭ መንግስታትን እንዲህ ስላደረጉ ኢንዲህ አደረግን
ለማለት ውሸታቸውን በቴሌቪዢን ቀጣጠሉና ዶክተር ታዬን አስራ አምስት ዓመት ፈረዱበት።
ከስንት ዓመት በሗላ ዛሬ ደሞ አኬልዳማ ብለው ውሸት በመቀጣጠል ንጹሀን ዜጎችን እስርቤት
ለማማቀቅ ሌላ የፕሮጋጋንዳ ትያትር ጀመሩ።
Page
2 of 3
ወያኔ በዚህ የቴሌቪዥን ድራማው ላይ በሀገርም በውጭም ያለውን ጋዜጠኛ ሁሉ ሽብርተኛ፤
የኢሳያስ ተላላኪ፤ ጠንካራ የፖለቲካ ድርጀቶችን ሁሉ ሽብርተኛ የሻእቢያ ተላለኪ፤ አልቃይዳ
አልሻባብ ምናምን እያለ ሊገናኙ የማይችሉትን ነገሮች ውሸት ወሬ እየፈተለና እየጎጎነ አንድ ላይ
ሊሰፋ ይሞክራል። መለስ ዜናዊ መራሹ ወያኔ የሻእቢያ ፍጡር ነው። በዚህ አንከራከርም። ጉዳይ
ፈጻሚ፤ ተላላኪ፤ እስከመጨረሻው የኤርትራ መገንጠል የትግራይን አርሶ አደር ልጆች በገፍና
በግፍ እየወሰደ በጦርነት ረመጥ እያገፋፈጠለት ሲያገለግል የነበረው አሽከር መለስ ዜናዊ መሆኑን
የማያውቅ ኢትዮጵያዊ ይኖር ይሆን
? ከተገነጠሉስ በሗላ? ኤርትራ የብቻ ኢትዮጵያን የጋራ
አድርገው፤ የህዝቡን ሀብት በሁለት አቅጣጫ ሲሰርቁ ኖረው ኖረው፤ በጥቅም ቢጋጩ የወያኔ
አሽከርነትና ተላላኪነት ቀረ። እግዚአብሄር ነው ኢትዮጵያን መከራ ይቀነስልሽ ሲላት ጣልቃ ገብቶ
ሁለቱን ያጣላልን። እኛማ ሀምሳ ዓመት ብንታገልም አናጣላቸውም ነበር። እንደ አሽከርየው
ክፋትና ታማኝነት ቢሆን። ያነው እንግዲህ ዛሬ አኬልዳማ ብሎ በቀጣጠለው ውሸት የቴሌቪዢን
ድራማ የሀገሪቱን ልጆች፤ አሸባሪዎች፤ የኢሳያስ ተላላኪዎች እያለ ስም የማጥፋቱን ፕሮፓጋንዳ
የተያያዘው። መልእክቱ ጋዜጠኞቹና ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶቹ ካሸባሪዎች ጋር ሆነው
የኢትዮጵያን ህዝብ ደም ሊያፋስሱ ያሴራሉ ነው። የኢትዮጵያን ህዝብ ደም አፍስሶ ያልበቃው
ወያኔ ነው።
የበደኖውንም እልቂት አምጥቶ አንድ ላይ ሰፍቶታል። ያድርጊት የወያኔና የኦነግ ቀጥነተኛ ስራ
ለመሆኑ የሚጠራጠር የኢትዮጵያ ህዝብ የለም። ሁለቱም ሰዎች ለ አማራው ህዝብ ያላቸው ስር
የሰደደ ጥላቻ የሚታወቅ ነው። በደኖ ገደል ውስጥ ከነህይወታቸው፤ ገሚስም እየታረዱ የተጣሉ
ህጻናትና ሴቶች ብቻ አይደሉም ያኢሰብዓዊ ድርጊት የተፈጸመባቸው። አሰቦት ደብረወገግ ገዳም
የነበሩ መነኮሳትም በህይወት ከገደል ላይ እየተጣሉ አልቀዋል። ይህ ሁሉ የሚደረገው የድርጊቱ
አዛዦች ኦነጎችና ወያኔዎች ሽግግር መንግስት ነን ብለው አብረው አዲስ አበባ ላይ ሽርጉድ ይሉ
የነበረ ጊዜ
1984 ላይ ነው።
የዚያን ድርጊት ፈጻሚዎች ለመያዝና ለፍርድ ለማቅረብ የተደረገ የልብ ሀሳብም ጥረትም
አልነበረም። በሁለቱም በኩል። ይልቅስ ወያኔ የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ዋና እሴት አድርጎት መልሶ
መልሶ ፊልሙን እያሳየን የኢትዮጵያን ህዝብ ያስለቅሳል በሀዘን ይጠብሳል። ያሳቅቃል። የአርሲ
አርባጉጉ እልቂትም በአማራው ላይ ያነጣጠረ ነበር። ወያኔም ኦነግም የተሳተፉበት መሆኑን ሁለቱ
ሲካሰሱ ግልጽ በሆነ ሁኔታ መረዳት ይቻላል። ማንም ይፈጽመው ማን ይህ ሁሉ በሰብዓዊ ፍጡራን
ላይ የደረሰው ዘግናኝ እልቂት ወያኔን ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ የገባ መሆኑን የሚጠራጠር
ኢትዮጵያዊ ይኖር ይሆን
? ታያዲያ ያንን ከሩቅ ቦታና ከሩቅ ጊዜ ጎትቶ አምጥቶ ከነግንቦት ሰባት
ጋር መስፋት፤ ካንድነት ፓርቲ ጋር መስፋት ፡ ከእስክንድር ነጋ ጋር ከነ አንዱዓለም አራጌ ጋር
መስፋት፤ ከነ ርእዮት አለሙ ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዢን ጋዜጠኞች ከነፋሲል የኔነህ ጋር
መስፋት፤ ከኢትዮሚዲያው አብርሀ በላይ ጋር መስፋት ምን አይነት ያይምሮ መሻገት የገጠመው
ሰው ያዘጋጀው ድራማ ነው
?
ህዝብን እያሸበሩ ሀያ አመታት ሙሉ በመግዛት ላይ ያሉ፤ የመንግስት ቅርጽ ይዘው የሚንቀሳቀሱ
ዘራፊዎችና ሌቦች፤ ወደ ስልጣን ከመጡ ጊዜ ጀምሮ ለጨፈጨፉት፤ ላስጨፈጨፉት፤
ላጨፋጨፉት ሁሉ ከተጠያቂነት እንደማያመልጡ ልባቸው ያውቀዋል። ሀረርጌ ወተር ላይ
የጨፈጨፉት፤ ደቡብ ውስጥ ባደባባይ የጨፈጨፉት ፤ ጋምቤላ በአኙዋኮች ላይ የተደረገው የዘር
ማጥፋት ዘመቻ፡ አዲስ አባባ ምርጫ ዘጠናሰባትን ተከትሎ የጨፈጨፉት ሌላውም ሁሉ
… እነዚህ
ታዲያ በየትኛው የሞራል ብቃታቸው ነው ሌላውን አገር ወዳድ ዜጋ አሸባሪ ብለው ባዘጋጁት
የደንቆሮ ድራማቸው የሚወነጅሉት ። የወያኔ መንግስት ገዳይነው። ጨፍጫፊነው። ዜጎችን
ያለምክንያት የሚያስር የሚያንገላታ ነው። የታወቀ ነገር ነው። አኬልዳማ ብለው ምን
አደከማቸው
? ማድረግ የሚፈልጉትን ማሰርም ሆነ መግደል ስራቸው ነው ለምን አያደርጉትም?
እስከዛሬ ሲያስሩና ሲገሉ ፈርተው ያውቃሉ
ባለፉት ሀያ አመታት ያደርጉት እንደነበረው ሁሉ አሁን የኢትዮጵያ ህዝብ ቢያንስ ለሁለት ነገር
መዘጋጀት አለበት። ወያኔ እንዲህ አይነት ፕሮፓጋንዳ መንዛት የሚጀምረው አንድ ነገር ለማድረግ
በዝግጅት ላይ ሲሆን ነው።
ምን ሊሆን ይችላል
No comments:
Post a Comment