Tuesday, December 20, 2011

የአዲስ ፎርቹን ‘‘ላይፍ ማተርስ’’ አምድ አዘጋጅ የሆነችው ሉሊት አምደማርያም ስልጣን ከለቀቁ

የዛሬ አምስትና ስድስት ዓመት ገዳማ ይመስለኛል ጠቅላይ ሚንስትራችን ስልጣን ለተተኪው ትውልልድ አስተላልፋለሁ ሲሉ የሰማች የአዲስ ፎርቹን ‘‘ላይፍ ማተርስ’’ አምድ አዘጋጅ የሆነችው ሉሊት አምደማርያም ስልጣን ከለቀቁ (ከልብ በማዘን ይመስለኛል) ‘ሚስ’ አድርጋቸዋለሁ ብላ የጻፍችውን ጽሁፍ ሳነብ በተለይ በምርጫው( 1997) ማግስት ስለነበረ ሃገራችን ውስጥ በተፈጠረው ሁኔታ ቆሽቴ እንዳላረረ ሁሉ መቸም መልካም አነጋገር ቁጣን ያበርዳል ነውና(በሉሊት አነጋገር አንጀቴ የራራ ቢመስለኝ)እኔም ቢሆን እንዲህ እንደዋዛ ስልጣንን ለህዝብ አሳልፈው እንደማይሰጡ እየተረዳሁት አውጥቸ አውርጀ ለራሴው አዎ የትኛቸውም ስራቸው ቢያመዝን (ክፉም አሊያም ደጉ ስራቸው) እንደመሪነታቸው እኔምኮ ሚስ አደርጋቸዋለሁ ግን ደግሞ ይልቀቁ! ይበቃቸዋል አልኩ በልቤ! ይህንኑ ለራሴ ጠይቄ የመለስኩትን ጥያቄ የቅርብ ጓደኛዬንም (ፅሁፉንም ፎርቹን ላይ ማንበቤንም ገልጨ) ስጠይቀው ጥያቄው ተገቢ አይደልም ምክንያቱም ‘‘ስልጣን እንዲህ በዋዛ የሚለቁ መሪ አይደሉም’’ አለኝ:: ግድየለህም እንደው ለሰክንድ ‘ቢሆን’ ብለህ አስብና አልኩት እሱም ‘‘ሰውየ ያምሃል’’ ብሎኝ ሲያርፍ ካልክ እሽ ብዬ ዝም አልኩ::
ከዛም ጥያቄየን ወደ ሉሊት ዓምድና ወደራሴ (እኔም ሚስ አደርጋቸዋለሁ ወዳልኩበት መልስ) መለስ አድርጌ ግን በኛ ሃገር ‘ክሪትካል የሆነ አስተሳሰብ የማይጎለብትው ለምንድነው?’ አልኩ ለራሴ ምክንያቱም ለዘመናት የገዙንን መሪ ከማሞካሼትና የስልጣን ዘመናቸው በተራዘመ ከምንል ለምን በለውጥ ማመን አቃተን በማለት:: ምክንያቱም ያ ባህላችን ቢሆን ሉሊትም ሆነች ሌሎች ባለሞያዎች ድክመቶችና ችግሮቻችን ላይ በማተኮር ተራማጅ የሆን አስተሳስብን በማራማድ ለተሻለች ሃገር ግንባታ ጉልህ አስተዋጸኦ ማድረግ ይቻል ነበር (በተለይ ደግሞ እንደወጣትነታችንና የሃገር ሃላፊነት ከታላላቆቻችን በበለጠ የኛ ድርሻ ሊሆን እንደሚገባው በማመን)::
ነገ ከዛሬስ እንደሚሻል እንዴት ማመንና ለተግባራዊነቱ መስራት አቃተን? አስራራችንና አስተሳሰባችንን ቀይረን የተሻለ ልብስ መልበስ ስንችል ለምን የተቀደደና እላቂ ልባስችንን እየጠቀምን መልበስን እንመርጣለን? ነው እንደተባለው የአስተሳሰባችን (አይ ኪው) ደረጃ ከሌሎች ሲነጻጸር አሁንም አናሳ ነው(!?
ከዚህ ጋር በተያያዘ ሳስታውሰው እስካሁን ድረስ አንድ የሚገርመኝ ደግሞ የመጀመሪያ ድግሪየን ከያዝኩብት ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የመጡ ምሁር ጥናታዊ ጽሁፋቸውን እንዲያቀርቡ አሁን በምማርበት ዩንቨርስቲ ተጋብዘው በተገኘሁበት ውስጥ ‘‘ለአፍሪካ በተለይ ደግሞ ለኢትዮዽያ ኋላቀርነት ቁልፍ ምክንያት የመልከዓምድራዊ አቀማመጥ ነው’’ ብለው ሊያስረዱ ሞከሩ:: ሲያብራሩም ‘‘አውሮፓውይን የተሻለ የመሬት አቀማመጥም ሆነ አየር ንብርት ስላላቸው የመሰረተ ልማት አውታሮችን በቀላሉ መዘርጋትና ማስፋፋት ችለዋል’’ አሉ:: ታዲያ ይህ አባባላቸው በኔ አመለካከት ራስን ነጻ ከማውጣት የተለየ አንደምታ አልነበረውም (ጨለማን ከመውቀስ ምን መለኮስ አይደል የሚባለውስ):: አብዛሃኛው ተሳታፊም ስዊድንያውያን አሊያም የስዊድንን የአየር ጸባይ የሚያቅ ስለነበር ታዝቦ ዝም ከማለት ውጪ በቀላሉ የሚዋጥላችው አይመስለኝም:: ምክንያቱም ስዊድንያውያን በጥረታቸው ባይሆን ኖሮ አይደልም ለሌላ ሃግር ርዳታ ለጋሽ መሆን መቻል(According to SIDA’s annual report ስዊድን ከአለም ዘጠነኛ ርዳታ ሰጭያጭን ነች ለምሳሌ በ2009 ሃምሳ ሚሊዮን USD በ2010 ደግሞ 42 ሚሊዮን USD የህዝብ ብዛታቸው ግን አንድ ዘጠነኛ) ያጋጠማቸውን ረሃብና ድርቅ (ከመቶ አመት በፊት ገዳማ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ህዝብ ማለትም ከጠቅላላው የህዝብ ብዛት ሃያ አምስት ፕርሰንቱ ወደ አሜሪካ ተሰዷል) እንዲሁም ለኑሮም ሆነ የግብርና ምርትን ለማምረት አመቺ ያልሆነ የበረዶ ወቅት መቋቋም ፈፅመው ባልቻሉ ነበር:: ለነገሩ የተፈጥሮ መልከዓምድር (አየር ንብረት) ከተነሳ አሁንም ቢሆን 43 ፐርሰንት ያክል ምግባቸውን ከውጭ ሃገር ያስገባሉ:: ይህም የሆነበት ምክንያት ለግብርና ተስማሚ የሚሆን መሬት(አየር ንብረት) ስለሌላቸው ነው:: ይህንን ይወቁ አያውቁ ባላቅም ስዊዲን ሃገር ሶስተኛ ድግሪያቸውን መያዛቸውን ኋላ ላይ ሰምቻለሁ::
ታዲያ እኛ የ13 ውር የፀሃይ ባለፀጋዎችና የወንዞችና ሃይቆች ባለቤት ለጋሽነት ቀርቶብን የልመና እጃችንን በመሰብሰብ ራሳችንን መመገብ እንዴት ለዘመናት ይሳነናል?
መንግስታችን የተስፋ መግቦት መቼም ሁሌ አያሳጣንምና ባለፈው ጥናታዊ ጽሁፌን ለመስራት አገር ቤት በሄድኩበት ሰዓት መስቀል አደባባይ በትልቅ ቢልቦርድ ላይ የጠቅላይ ሚንስትሩን ምስል የያዝና ‘‘ልመናን ለመጪው ትውልድ አናውርስም’’ የሚል ፅሁፍ ያለበትን አነበብኩ:: ምን ማለት እነደሆን ሳወጣ ሳወርድ በተለይ ደግሞ አሁን አሁን በማነበው ዘገባም ሆነ በሄድኩበት ሴምናር ኮንፈርንስ ሁሉ ሃገራችን በሚሰጣት ምፅዋት ከአፍሪካ(ከአለም?) አንደኛ ናት የሚለውን ማስረጃ በማሰላሰል ሁሉንም በልመና የመጣ ገንዝብ የመንግስትን አቅምና ስልጣን ለማጎልበት አሊያም በሙስና ተጠቅምን እንጨርሰዋልን የማስተረፍና የማስተላለፍ ግዴታ የለብንም ማለት ይሆን እላለሁ:: ታዲያ ምናቸውን ይሆን እኔና ሉሊት ሚስ የምናደርጋቸው ተለምኖ የመጣን (በተራበ ህዝብ ስም) ሳይቀር ለሚመዘብሩ መሪ?
ሙስናና የህዝብን ሃብት ከህዝብ ፍላጎትና ጥቅም ውጪ ማባከን በሚመለከት ከላይ የጠቀስኳቸውና በሃሳባቸው ያልተስማማሁባቸው ምሁር አሁንም ጎረቤት ኬንያን አሃዝ ሳይቀራቸው የፓርላማ አባላት ለግል ጥቅም የሚያውሉትን የህዝብ ሃብት ጠቅሰው ሃገራችንን ነፃ ለማድረግ ይመስላል ዝም ብለው አለፉ::
ለነገሩ እውነትን ለምን አልተናገሩም አይደለም የኔ ችግር:: ያልሆነ ስምና ዝና በመስጠት የህዝብ አገልጋዮችን ለድርጊታቸው ተጠያቂ እንዳይሆኑ ሳይጠየቁ መከላከያ ከመሆን ባሻገር ለህዝባ ለወግን ተቆርቋሪ ኢትዮያዊያኖችን ማስጠቆርም ጭምር ስለሚሆን እንጅ::
የሉሊትም ጽሁፍ ቢሆን እንደነ ርዮት አለሙ አይነትን ሃገር ወዳድና የወደፈት ተስፋ ከማሳዘን አልፎ ያለዕዳቸው ፅዋ እንዲከፍሉ የበኩሉን አስተዋጸኦ ያደርጋል:: በርግጥ ያ ረዳት ፕሮፌሰርም (ከላይ የጠቀስኳቸው) ‘አፍ እላፊ’ ቢናገሩ ስራቸውን ማጣት ከባሰም ዘብጥያ ይጠብቃቸው ይሆናል:: ሉሊትም ሲመስልኝ ‘‘ላይፋ ማተር’’ ነውና ይህንኑ ጠንቅቃ ስለምታቅ እንጅ ዕውነት የሃገራችን ውደቅትና የእንብርክክ መሄድ የተሰወረባት አይመስለኝም:: በተለይ ደግሞ አሜሪካ እንደማደግና እንደመማሯ(!) ምክንያቱም እዛ ሃገር ከፈጣሪ በታች የሆነው ነገር ሁሉ አለና(ፈጣሪ ለሰው ልጅ በሰውነቱ የሰጠውና አይጠቅምህም ብሎ ያልሰጠውም መብት ሳይቀር)::
እናም ያም ሆነ ይህ የኔ(ምናልባትም የሉሊትም ጭምር) ጥያቄ የሚሆነው መሪያችንን ‘‘ሚስ’’ የምናደርጋቸው መቼ ነው? ከሚቀጥለው ምርጫ በኋላ ወይስ ዕድሜ ከሰጠንና የእሳቸውን እድሜ ስንደርስበት ምክንያቱም ያኔ ሁላችንም ልንኖር አንችልም… ብንኖርም አንድ ሃገር የምንኖር አይመስለኝም:: በርግጥ የዛኔ ጓደኛየም (ከላይ ጠይቄው ‘‘ጥያቄው ተገቢ ጥያቄ አይደለም’’ ያለኝ) ሚስ ያድርጋቸው አያድርጋቸው ይነግረኝ ይሆናል::
ደግሞ ራት አብረን እንድንበላ የማይፈቅዱ አሊያም አብሮን እንዲበላ የማንፈቅድለት ሰው በምን መልኩ ሚስ ሊደረግ ይችላል?ብቻውን የበላ ብቻውን ይሞታል አይደል የሚለው ያገሬ ሰው… ዕድሜ ይስጠን ለማንኛውም!!
ይህንን ትዝብት ለማንሳት ያስገደደኝ ሁሌ በተለይ ደግሞ የሃገራችን ህዝብ ጉስቁልና እንግልትና ስደት ብሎም ከሰው በታች መሆንን በብሶትና በቁጭት የሚችሉትን ያክል አስተዋጽዖ ለማደረግ በሚጥሩ ሰዎች ላይ አዛኝ ቂቤ አንጓች እንዲሉ ህዝባችን የለም አልተራበም! አልተበደልም! አልተከፋም! አልታርዝም! የሚሉና ወገባቸውን ይዘው የሚከራከሩ በሄድኩበት ሁሉ ሲግጥመኝ አስተውላለሁ:: ደግሞ የሚያሳዝንው በውጭ ሃገር አገር ውስጥም ከሆነ በህዝብ ሃብት የሚንፈራሰሱ መሆናቸውና ርሃብ ማለት ምን ማለት እንደሆን በትክክል ማብራራት የማይችሉ ግለሰቦች ናቸው:: አላደገችም ግን እንደሱ እንደሚሉት ሃገራችን አድጋለች ይባልና ግን የበለጥ እንድታድግ መመኘትና መጣር ምኑ ላይ ነው መጥፎነቱ? ለምንስ መከራከር አስፈለገ?
አሁን አሁንማ የአይ ኪው’አችንን ነገር በጣም እንዳጤነው በቂ ምክንይት እያገኘሁ ነው። በተለይ አሜሪካ ውስጥ በሚገኝ አንድ ዩንቨርሲቲ በተሳተፍኩበት ሴሚና ላይ ታዳጊ ሃገራት (ከቻይና ወጪ) ዝቅተኛ አይ ኪው አላቸው ሲባል ከሰማሁ ወዲህ እውነትም እያልኩ ነው! የኢትዮጵያዊያንማ ደግሞ ከሁሉም ያንሳል ሲባል ከዛ በፊት ይፍ የሆን ጥናት አለ ሲባል ሰምቻለሁ(?)አዎ የኛ የማሰብ ደረጃ አናሳ መባል ቢያናደኝም ግና ደግሞ ከማየውና ከምዳሰው የሃገሬ መደህየት አይበልጥብኝም! ለምን አፍሪካ በተለይ ደግሞ ሃገራችን መለወጥ አልቻለችም?
በጣም የሚገርመው ከነኝሁ ከሰማንያ ያላነሱና ከተለያዩ የሰሜን አሜሪካ ዩንቨርስቲ ከተውጣጡ የሁለተኛ ድግሪ ተማሪዎች ውስጥ ሁሉም በተመሳሳይ ድምፅ አሜሪካን ያክል የሚመራን መንግስት ‘‘መንግስት የሚገባውን ያክልና የተጣለበትን ሃላፊነት አልተወጣም’’ በማለት ሲያብጠለጥሉት ስሰማና የኛን ሃገር ‘‘ሁሉ ሞልቶ ተርፎ’’ ዲስኩር ሲባዛም መሪያችን የተለየ ፍጡር ነው አሊያም ደግሞ ቅንድቡ (መልኩ) ሳይቀር ሲሞገስ ሲዘፈንለት በዚህ ዘመን መስማት ለኔ አሁንም ትልቅ የሆነ ችግር አለብን የሚለው አስተሳሰብ ያይልብኛል….
በመጨረሻ ቁጭቴን ለመቋጨት ያክል ሌላኛውና ብቻይን ሆኘ ስለሃገሬ መሻሻል ሳስብ ለተግባራዊነታቸው (በተለይ አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት) በጣም ምናባዊና አንዳንዴም ለራሴው ቅዠት እስኪመስለኝ ፈፅመው የማይቻሉ የሚመስሉ ሁለት መሰራታዊ የመፍትሄ ሃሳቦች ይታዩኛል:: ፩ኛ መንግስት በሰላማዊ መልኩና ያለምንም ማንገራገር ስልጣንን ለህዝብ መስጠት ፪ኛ ውጭ ሃገር በተለያየ ምክንያት ወጥተው በተለያየ የሙያ መስክ ያሉ ኢትዮጵያዊያን(ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጨምሮ) ሁኔታዎች ሃገሪቱ በምትችለው መልኩ ተመቻችቶላቸው እንደግዴታ ወደሃገር በመመለስ ቢቻል ቀሪ የህይወት ዘመናቸውን ባይቻል ደግሞ ለተወሰነና ረዘም ላል ጊዜ ማገልገል አማራጭ የሌለው ግዴታ ቢሆን…
ለሃገራችን የሚበጀውን ሁሉ ፈጣሪ ያምጣልን ኢትዮጵያም ለዘላለም ትኑር!!

No comments:

Post a Comment