መለስ እና ጋዳፊ
ከመላኩ ፀጋዬ መኮንን
በአንድ ሃገር ውስጥ ባለጌዎች እና ስድ አደጎች ስልጣን በጃቸው ሲገባ በምን መልክ አላግባብ እንደሚጠቀሙበት ብዙ ሩቅ ሳንባክን ከቀድሞው የዩጋንዳው ኢዲያሚን ዳዳ ዓንድ ብለን እስከ አቶ መለስ ዜናው አስረስ በየሃገራቱ የተፈጸሙትን ኢሰብአዊ ድርጊቶች ብንመለከትት ስለአምባገነኖች አገዛዝ ምንነት በቂ ማስረጃ ነው። በወዲ መለስ አገዛዝ በበረሃ ዘመናቸው አንስቶ የፈጸሙትናን ለከት ያጣ ርህራሄ የለሽ ተግባራቸው ይኽውና ለሃያ አመታት የያዝነው፤ ያየነው፤ የስቃይና የመከራ፤ የስደት፤ የሞት፤ የእስራት፤ የቸነፈርና የረሀብ እገዛዝ ዘክረውናል። አሁን ግን ይህ የሰቆቃ ኑሮ ወደዱም ጠሉም ለመጨረሻው ጊዜ መወገድ አለበት። የተቀመጡበት ወንበር ሲቆረቁረወት ካልተሰማወት ሊፈነግለወት ወስኞል ፤ውሳኔውን ባደባባይ እንዳይገልፅ ለጊዜው በብዙ ባላ ሊያስደግፉት እየሞከሩ ነው ይህ ሂደት አንቅሮ ከተፋወት ህዝብ ግፊት እስከመጨረሻው ሊደግፈወት አይችልም ፡፡ ለመደገፊያ ያውሸለሸሉት መሰላል ቀድሞ መበስበሱን ተረድተው እና ሕዝብ አንቅሮ የተፋወት መሆኑን አውቀው በጊዜ የመቋጠሪያ ውሉ ሳይጠፋ መሰስ ይበሉ፡፡
ሕዝቡ ከቀን አንድ ጀምሮ አንቅሮ ተፍቶወታል፤ እንደ እንሰሳ ሰው የተፋውን መልሶ አይውጥም አራት ነጥብ አይደል የሚሉት፡፡የማቆሚያ ነጥብ የሚያውቁ ስለሆነ ሕዝቡ ከአራት ነጥብ አልፎ ሃያ ነጥብ ብሏል። ታዲያ ሳልሞት አልወርድም የሚለውን የአምባ ገነኖች የሞኝ ዘፈን ትተው ሾለክ ቢሉ ለእርሰዎም ሆነ ለሀገሪቱ በጣም የተሻለ ነው።ለነገሩ የእርሰወ አይነት አገዛዝ የሚከተሉት ከራሳቸው ፍላጎት ውጭ ለሌላው ደንታ ቢስ መሆናቸውን አሁን በትኩሱ ጋዳፊ በልጆቹ ላይ ሳይቀር እልቂት እንዲፈጸምባቸው ያደረገ በመሆኑ ውሳኔወን በምን ላይ አንደሚያሳርፉ ለእርሰወ ልተወው፡ ግን ከታሪከው ሽርፍራፊ እንደምራዳው በሸር እንጂ በጀግንነት ወይም በሞገደኝነት ስለማይታሙ አራዳው የአስረስ ልጅ ቀኑን መዝኖ መሰስ ይላል የሚል ግምት አለኝ፡ ለማንኛውም ጊዜ ውሳኔ ይሰጣል፤ አሁን የተማመኑበት የዘር ጥርቅም ሲናድ በዚይን ጊዜ የእርሰወ ወኔ ይታያል፤ለነገሩ በቅርብ የሚያውቀወት ታጋዳሊ ሳይቀር በዋሉበት የጦር ግንባር ከድጋይ ስር ከመወተፍ ውጭ ቆምጨጭ ያለ ውሎ እንደማይሆንለወት ከግንባር አባሎቸወ የሚነገርለወ የታሪክ ባለድርሻ ነወት።
የሽወዳ አገዛዝ፡የግድያ አገዛዝ፤ የከፋፍለህ ግዛ አጋዛዝ ከአንድ ጎሳ የተውጣጡ የቀን ጅብ ግለሰቦች ጥርቅም እንካ ስላንቲያም ማቆሚያው ዘመን ላይ ደረስን፤ ምንም የብረት አጥር ቢያከማቹ፤ በቀውላላና ደረተ ሰፊ ዘበኛ ቢሸፈኑ፡ ገልጦ ሊያይ የሚችለውን የሕዝብ አይን ተከልለው ሊያመልጡ አይችሉም፤ለዚህ አብነት ብዙ ሳንርቅ የአንድ ወቅት የጡት አባተወን የሟመር ጋዳፊን ምስል ይመልክቱ። ሰው ነወትና በ1997 ምርጫ ማግስት በሰላማዊ ሰልፍ የወጡትና በየጎዳናው ኳስ ለማንጓትና ከትምህርት ቤት ደብተራቸውን እንዳነገቡ በአነጣጥሮ ተኳሽ ድረትና ጭንቅላታቸውን ያስፈጇቸው ንጹሃን ወጣቶች ደም ሲፋረድወና መላከ ሞት ሳያስቡት በድንገት ደርሶ እንደ ጋዳፊ ጭንቅላተወት በጥይት ሲያፈርሰው፤ ደረተወት በጥይት ሲሰነጠቅ ሲመለከቱ አፈወትን ብቻ ሳይሆን የተቀመጡበትን የሚሊሊክ ቤተመንግስት ሳቀር ደም ደም እየሸተተው በመምጣት ላይ መሆኑን የማረጋገጫ መልክት ደርሶወታል።
ከሟመር ጋዳፊ የበለጠ በነጭ ለባሽ የተከበበ፡በሰራዊት የታጠረ ሞትንን ለመከላከል ባንከር ሳይቀር የሰራ ማደሪያው የተሰወረ እንዳልነበር ከርሰወ የበለጠ ማን በቅርብ ያውቀዋል፤ ለምን ቢባል በአንድ ወቅት የሊቢያ ዝምድና እንዳለወት ለሟች ጋዳፊ ሹክ እስከማለት የቀረበ ዝምድና ነበራችሁ ብየነው፡ለማንኛውም የጋዳፊ ጦር ከለላና የስለላ አጥሩ ከንቱ ጥረት ከሕዝብ እይታ ግን አልጠበቃቸውም፤ ከብዙ ጥፋት በሃላ የማይቀረውን ጽዋ ተጎነጩት ፤ትናንት አይጥ ምናምንቴ እያሉ ወደታች የገፏቸው ተቃዋሚዎችም ዛሬ እንዳይጥ ሆነው በሏቸው፣እንደ ሲቢአኤስ ዘገባ ከሆነማ ጋዳፊን የመጨረሻ ጽዋ ያጠጣቸው የራሳቸው ጠባቂ እንደሆንም የዜና ምንጮች እየጠቆሙ ነው፡በዘበኛ መጠበቅን በጦር ሰራዊት መተማመንን ትክሻ ላደረጉት አቶ መለስ ዜናዊ፡ ለግብረ በሎቹና ለስለላ ሃላፊዎቹ ለነአቶ ጌታቸው አሰፋ ደግሞ ይበልጥ የራስ መርዘን የለቀቀ ጉዳይ ነው፡ ለምን ቢባል በዚህ ወቅት ማን ይታማናልና ነው። እንዲሁ በስጋት ከራስ ጥላ ጅምሮ በየደቂቃው መሞት፤መሞት መሞት... ቀኑ መሽቶ እስኪነጋ መሸማቀቅ የቀኑን በሲጋራ የሌሊቱን በአልኮል መደንዘዝ የተጋዳይ መለስ ኑሮ እስከመቸ እንደዚ ይቀጥላል፤ ህዝቡን ብቻ ሳይሆን እራሰወትንም ነጻ ለማውጣት ቆራጥ ውሳኔ መድረስ አዋቂነት እንጂ ጅልነት አይደለም።
አቶ መለስ የሕዝብን ጥያቄ አድበስብሶ ሰላማዊ ኑሮን አኮስሶ የራስናን የአጋሮችን ኪስ አደጉሶ ብቻ የማይኖሩበት ዘመን ደርሰዋል፤ለምሳሌ የቤንሻጉልና ጉሙዝ ገዥ የነበረው ያረጋል አይሸሽም ብቻ 83 ሚሊዮን ብር መዘበረ የሚል ዜና ሲሰማ አጀብ ጉድ ቀዳማዊ ዘራፍ ውይዘሮ አዜብ መስፍንን ጨምሮ በላይኛወቹ ምን ያህል ተዘርፏል የሚለውን መገመት አያዳግትም። ዋናወቹ ሰወች እማ ዘረፋው በብር ሳይሆን በዶላር ለመሆኑ የአለም ባንክ ስምንት ቢሊዮን ዶላር በእርሰው አገዛዝ መውጣቱን ይፋ አድርጓል፡፡ቁም ነገሩ ማን ምን ያህል ደርሶታል የሚለውን የአንበሶቹን ድርሻ ለማወቅ ነው ጉጉቱ እንጅ አገዛዘወ የዘረፋ ለመሆኑ የታወቀ ነው፤ የሚገርመው ዘራፊወቹ ያሸሹትን የህዝብ ገንዘብ ሳየጠቀሙበት መቅረታቸውን መገንዘብ አለመቻላቸው ብኩንነት ምን አይነት አደንዛዝ መሆኑ ነው የሚያመለክተው፤ ዛሬ ሽብርተኛ እገሌ መሌ እያሉ ስም በመለጠፍ እስር ቤት በነ ተዘራ ቦጋለ፤ ሞኒ መንገሻ፤ ሰይድ አሊ በመሰሰሉት አረመኔዎች የቁም ሰቃይ የሚያዬት ኢትዮጵያዊያን ዘመን የማይሽረው የታሪክ ባለውለታ ዜጎች መካከል ግንባር ቀደሞቹ እንደሆኑ በሚገባ ያውቁታል፤ ደፋሩ የሙያ ባልደረባየና የአንድ ወቅት አለቃየ የነበረው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በግልጽ እንደነገረዎ በክብር መውረድና የጣሉትን
የተበላሸ ታሪክ አድሰው ከስልጣን መሰናበት ወይም የምስሩ 32 አመት ገዥ ሙባረክ ካለያም ከከፋ ደግሞ የጋዳፊ እጣ በእጀወ ይሽከረከራል፤ምርጫው የእርሰወ ነው፡ሕዝቡ ግን ያለጥርጥር የወሰነ መሆኑን ይወቁት አራት ነጥብ።
መቸም እርሰወ በጣም መጸሐፍ አንባቢ መሆነወትን ወይዘሮ አዜብን ጨምሮ አንዳዶች ሲመሰክሩ ሰምቻለሁ ነገሩ ያይጥ ምስክሯ ድንቢጥ አይደል የሚባለው አየ የኔ ነገር ደሞ የማይወዱትን ያማራ ተረት ደነቀርኩበወ ለማንኛውም ወዲ ዜናዊ በነጠረ እይነወና ልምደዎ ይችን እየተጎነጩ እንደሚያነቧት ተስፋዬ የላቀ ነው ወይም በማለዳ ማን ምን አለ ብሎ ወሬ የሚያቀብለወ ጌታቸው አሰፋ በኩል ይደርሰወታል መልካም እድል።
ጸባይ ባይበድለን መሪ ብንታደግ፤
ለም ነበርሽ አንቺ አገር ሰርተንም ለማደግ፤
ዘመን ተቆጠረ ሄደ ገሰገሰ፤
በኢትዮጵያ ምድር ብዙ ሰው ነገሰ፤
ብዙ ብዙ ብሎ ከመለስ ደረሰ
ዘመን ዘመን ሽሮ በሌላ ሲተካ፤
ተስፋ እየጣልንበት ብሩህ እንዲፈካ፤
እያደረ ሲሄድ ሁሉ ተበላሽቶ በጥይት ተቦካ፤
ምን ብንረገም ነው እንዲህ አይነት ጣጣ
ተስፋችን ጨለመ የባሰው ሰው መጣ፤
ወይ ጥይት ጠብመንጃ ቀረ ውለታቸው፤
አገር ከመጠበቅ ከቤቱ አዋላቸው፤
አንተ ባለአፈሙዝ እሳት የጎረስከው፤
ለወገንህ መጉጃ ጥይት ያነገብከው፤
እባክህ ተመከር በስላሴ እንበልህ፤
የተቀመጥክበት አፈሩ ቢከብድህ
በድንገት ይኽ ቀን አንዳይናድብህ፤
ጥይትክን አዙረው ጠላትክን ለይና
መታዘዝ ይቅርብህ ለወገን አፈና
በጥይት መገዛት ይበቃናልና
አልተረዳህ እንደሁ የኔው ቢጤ ምስኪን
ላስረዳህ እውነቱን ወገን መበደልክን
ለእለት ጉርሻ ብለህ ሀገር ማስበተንክን
ብትችል አዙርበት ባትችል ጥለኽው ሂድ
ተሸኮሞ ሲጓዝ ይያዛል ያንተው ጉድ።
No comments:
Post a Comment