Monday, November 28, 2011

ባሇ ሐይኩ ሲጠየቅ

ባሇ ሐይኩ ሲጠየቅ
በታሪኩ ኃይለ
tariku_1998@yahoo.com
ሩባይ 1
ሃሳብ ከዛማ ተቃኝቶ ቃሌ ከብራና ተዋዯዯ
ምጥ ያክትሞት ሞቱን ሞቶ ወዲሇመኖር ተሰዯዯ
ረቂቃን ምስሌ ከሥተው ኅያዋን ጉለሓን ሆኑ
ነፍሴ ማኅላት ቆመች እሰይ ሩባይ ተወሇዯ
የዓሇማየሁ ሩባያት ገጽ 1
ሰሞኑን BETSY AND THE SUPERCOPTER በሚሌ ርእስ አዱስ መጽሐፍ በእንግሉዜኛ ቋንቋ ሇኅትመት በቅቷሌ። ዯራሲው ዓሇማየሁ ታዬ ከዙህ ቀዯም ባሳተማቸውና "የዓሇማየሁ ሩባያት"፤ "ግራፊቲ" እና "ሐይኩ" በተሰኙ የግጥም መዴበሌ መጽሐፎች እንዱሁም "ጣፋጭ ተረቶች" በሚሌ ርእስ ባሳተመው ትርጉም የህጻናት መጽሐፍ እናውቀዋሇን። በአዱስ አበባ ዩኒቨርስቲና በህንዴ ፑኔ ዩኒቨርስቲ በሥነጽሁፍና ሳይኮልጂ አሁንም በአሜሪካ የተሇያዩ ኮላጆች ትምህርቱን በመከታተሌ ሊይ የሚገኘው ዓሇማየሁ ታዬ ኢትዮጵያ ውስጥ በሬዱዮና በኅትመት ጋዛጠኝነት ሰርቷሌ ። በአሁኑ ወቅት በልስ አንጀሇስ ከተማ ቪላጅ ግላን ዌስት በተሰኘ ትምህርት ቤት በረዲት አስተማሪነት/ Teacher’s Aide/ በመስራት ሊይ ይገኛሌ። የአዱሲቱ መጽሐፍ ሇኅትመት መብቃት ምክንያት ሆኖኝ በገጣሚው ስራዎች ሊይ ያዯረግነውን ሰፋ ያሇ ቃሇምሌሌስ እነሆ!
ታሪኩ፦ የመጀመርያ ስራህ በሆነችው በዓሇማየሁ ሩባያት ጥያቄዬን ሌጀምርና እንዯው ሩባያትን ሇመጻፍ መነሻህ ምን ነበረ?
ዓሇማየሁ፦ እሷን መጽሐፍ ስጽፍ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ነበርኩ። አብዚኛውን ግዛዬንም የማሳሌፈው በማንበብ በመመርመር እና በመጠየቅ ነበር። በተሇይ ሇየት ያሇ ያጻጻፍ ስሌት የመሞከር ብርቱ ፍሊጎትም ውስጤ ነበረ። በወቅቱ የአቤ ጉበኛን ስራዎች እያዯንኩ አነባቸውና አጠናቸው ነበር። ታዱያ አቤ ጉበኛ የጻፋቸውን ሩባይ መሰሌ ግጥሞች ማንበቤና በአጋጣሚ ዯግሞ ፊዜጄራሌዴ በእንግሉዜኛ ያ዗ጋጀውን የዐመር ኻያም ሩባያት ማግኘቴ እንዱሁም ጋሽ ተስፋዬ የተረጎሙትን መሌክዏ ዐመር መጽሐፍ በፍቅር መውዯዳ ሩባያትን ወዯ መሞከር የገፋፋኝ ይመስሇኛሌ።
ታሪኩ፦ አቤ ጉበኛ ሩባያት ጽፏሌ ማሇት ነው?
ዓሇማየሁ፦ አቤ ሩባያትን መሰረት አዴርጎ የሩባይን ቅርጻዊ ስርዓት ተከትል በራሱ መንገዴ በርካታ ባሊምስት መስመር ግጥሞችን ጽፏሌ።
ታሪኩ፦ ሩባይ ሲነሳ አብሮ የሚነሳ ዐመር ኻያም መሆኑንና ይህ የግጥም ቤት የዐመር ቤት ግጥም እስከመባሌ መዴረሱን በመጽሐፍህ መግቢያ ሊይ አብራርተሃሌ። እስቲ ስሇ ሩባይ አጀማመርና ስሊጻጻፉ ትንሽ የምትሇን ካሇህ?
ዓሇማየሁ፦ የፋርስ ሰዎች ሩባይ መጻፍ የጀመሩት ጥንት ነው። ከዐመር ኻያም በፊት በርካታ ባሇቅኔዎች ሩባያት ጽፈዋሌ። ዐመር ኻያም ተጠቃሽ የሩባይ ዯራሲ የተባሇው በርካታ ሩባያት በመጻፉ ስራዎቹም ከፍተኛ ኪናዊ ዋጋ ስሊሊቸው እንዱሁም ተተርጉመው በመሊው ዓሇም በመነበባቸው ምክንያት ነው። አጻጻፉን በተመሇከተ ሩባያት ባሊራት መስመር ግጥሞች ናቸው። አንዴን ስራ ሩባይ የሚያሰኘው የቅርጽ እንጂ የይ዗ት ጉዲይ አይዯሇም። ሩባይ የራሱ የሆነ ሌዩ ቅርጻዊ አሰዲዯር አሇው።ይህም ከሶስተኛው ስንኝ በስተቀር ሁለም ስንኞች ቤት መምታቸው ነው። የሶስተኛው ስንኝ ከላልቹ ስንኞች ጋር ተስማሚ ዴምጽ አሇመስጠት ሩባይን ከላልች ባሊራት መስመር ግጥሞች ይሇየዋሌ።የመጀመርያው የሩባይ ጸሐፊ የግጥሙን አዯናቃፊ ዛማ ከአንዴ ህጻን ሌቅሶ እንዯቀዲው ይነገራሌ።
ታሪኩ፦ ሁሇተኛውን የሩባያት ስብስብህን መቼ ነው የምናነበው?
ዓሇማየሁ፦ የዓሇማየሁ ሩባያት ከታተመ በኋሊ ላሊ ሩባይ አሌጻፍኩም። አሮጌውንና የሇመዴከውን ነገር ተወት ካሊረከው ሐዱስ ብርሃን አይሊክሌህም ስሇዙህ ሐዱስ ብርሃን ፍሇጋ ሩባይን እርግፍ አዴርጌ ተውኩት። አንዲንዳ በህሌሜም ይሁን በታህተ ህሉናዬ ሩባያት ተወሌዯው በመንፈሴ ይዯመጡኛሌ፤ ግን አሌጽፋቸውም። በቸሌተኝነት እ዗ጋቸዋሇሁ። እናም ሁሇተኛ የሩባይ ስብስብ አሁን የሇኝም። ወዯፊት ግን ምናሌባት ሩባያትን እመሇስበት ይሆናሌ።
የዯመና ግሊጭ
የክረምት ሰማይ
ዯመና ዯፍኖ
ጭጋግ ጨፍኖ
ፀሃይ በዯመና ግሊጭ
ተሠርቃ
አንገቷን አስግጋ
አይኗን አጮሌጋ
አንዲፍታ!
ባይናፋር ብርሃን ብትጣቀስ
ምዴር
ብትን ብሊ ተሽኮረመመች።
ግራፊቲ ገጽ 16
ታሪኩ፦ ከ ሩባያት ቀጥል ያሳተምከው መጽሐፍ ግራፊቲ ነው። ሇምን የመጽሐፉን ርእስ ግራፊቲ አሌከው?
ዓሇማየሁ፦ ርእሱን ግራፊቲ ያሌኩት ቃለ ግራፊቲ በአንባቢዎቼ ሌቦና ውስጥ በጉሌኅ እንዱታተም ነው። ግራፊቲ እያሌኩ የምጽፋቸው ጽሑፎች የራሳቸው የሆነ ኪናዊ ስነጽሁፋዊና ስነሌቦናዊ ዲራ አሊቸው። የጥበብ አምሊክ ፈቃደ ሆኖ ግራፊቲዎቼን ወጥ በሆነ ዯረጃና በተብራራ ሁኔታ ይዤ እስክቀርብ ዴረስ በየመጽሐፎቼ ሊይ በተዯራቢነት የሚወጡት ነገርዬዎች ካንባቢ ጋር ተዋውቀዋሌ።
ግራፊቲ
The moon was really far, but warm and jolly; talking to me all night long she disappeared at dawn even before I get the chance to say "ciao gorgeous!" this winter
ግራፊቲ ገጽ 13
ታሪኩ፦ በግራፊቲ ውስጥ ያሳተምካቸው ግጥሞች ትንሽ ሇየት ያለና ያሌተሇመደ ይመስሊለ ፤ የራስህ የሆነ የአገጣጣም ብሌሃት እያዲበርክ የራስህ የሆነ አንባቢም እያፈራህ ያሇ ይመስሊሌ። አዱስ ነገር ሁሌ ጊዛም አስቸጋሪነት አሇውና ከአንባቢዎች ያገኘኸው አቀባበሌ ምን ይመስሊሌ?
ዓሇማየሁ፦ ግራፊቲ ውስጥ የተሇያየ ቅርጽና ይ዗ት ያሇቸው ግጥሞች ታትመዋሌ። ከሶስት መቶ በሊይ ከሚሆኑ የግጥም ስብስቦቼ መሃሌ መርጬ ነው ያቺን መጽሐፍ ያ዗ጋጀሁት። ግጥም መጻፍ ስጀምር ከሞከርኳቸው በርካታ ስራዎች መካከሌ ሇአብነት ያህሌ በትንሹ፤ የግጥም አጻጻፍ ስርዓት ከገባኝ በኋሊ ከሞከርኳቸው ስራዎች በጥቂቱ ከዙያ በኋሊ ዯግሞ ከመዯበኛው ያገጣጠም ስርዓት ካፈነገጥኩባቸው ስራዎች በከፊሌ አዴርጌ ነው ግራፊቲን ያሳተምኩት። ዗መኑ የቴክኖልጂ
የኢንተርኔት ዗መን ነውና ግራፊቲን በተመሇከተ እጅግ በጣም በርካታ አስተያየቶች በአካሌም ሆነ በኢሜሌ ዯርሰውኛሌ። አንዲንድቹ ግጥሞቼን እንዯወዯዶቸው ነግረውኛሌ። እነዙህ ቀሽም ግጥሞች ናቸው ያለም ይኖራለ። በዙህ አጋጣሚ ግጥሞቼን አንብበው የተሰማቸውን በኢሜሌም ሆነ በአካሌ እንዱሁም በተሇያዩ መገናኛ ብዘሃን ሊካፈለኝ ሁለ ምስጋናዬን አቀርባሇሁ።
ታሪኩ፦ ግራፊቲ ውስጥ በጻፍካቸው አንዲንዴ ግጥሞች ውስጥ በተሇምድ /taboo/ አይነኬ የተሰኙ ቃሊት ተጠቅመሃሌ በግጥም አጻጻፍ ዯንብ ይህ ተገቢ ነው ትሊሇህ?
ዓሇማየሁ፦ የገጣሚ ዋነኛ መሳርያ ቃሊት ናቸው። የተኮረኮረበትን ፍሌስፍናውን ህሌሙን ራእዩን ገጣሚ የሚያስተሊሌፈው በቃሊት ነው። ቃሊት በግጥም ውስጥ ከተራ ቃሌነታቸው በሊይ እጅግ የረቀቀና የዯመቀ ትርጓሜ አሊቸው። እንዯ አውዯምንባባቸው እንዯ ማህበራዊና ተሇምዶዊ አገባባቸው አንዲንዴ ቃሊት ከተራ ቃሌነታቸው አሌፈው ቱባ መሌእክት ያስተሊሌፋለ። እናም ቃሊት በግጥም ውስጥ ወሳኝ የሆነ ትርጉም፥ አስፈሊጊነትና ተገቢነት እንዲሊቸው አንባቢ ሌብ ማሇት አሇበት። እኔም አሁን ያሌካቸውን አይነት ታቡ መሰሌ ግን ተሇምዶዊ የሆኑ ቃሊት ስጠቀም ግጥሙን ከጻፍኩበት አጠቃሊይ መንፈስ ጋር እጅግ የተቆራኘና ሉሇያይ የማይችሌ ተዚምድ ስሊሊቸው ነው።
ግራፊቲ
I have only one lover, because it is costly to have three, አንዶም ፍቅሬ እንፋልት ናት እንዲሊቅፋት ምትሃት ናት እንዲሌ዗ነጋት ውጋት ናት ብርሃን ጨረር እሳት አሊት, then it is better to let go እንፋልት and move on to love three, when one evaporates, the other may blossom, if the blossomed falls, a stranger may appear and so on and so forth…
Haiku page 40
ታሪኩ፦ በግጥም ስራዎች ሊይ አርትዖት ሉዯረግበት ይገባሌ ትሊሇህ?
ዓሇማየሁ፦ ግጥም እጅግ ግሊዊ የሆነ ከገጣሚው ሰብእና አስተሳሰብ አስተዲዯግ ባህሊዊ እውቀት የንባብ ሌምዴ የማፈንገጥ ወይም ያሇማፈንገጥ ዜንባላ ወ዗ተ ጋር የተያያ዗ የስነጽሁፍ ዗ርፍ ነው። በወጉ የተጻፈን የአንዴን ሰው ግጥም ላሊ ሰው ሊርም ብል መነሳት ነውር ነው። የገጣሚውን የነፍስ ዛማ የቋንቋ አጠቃቀም ብሌሃትና ምርጫ የአሰነኛኘት ውርዴና የአመሇካከት አቅጣጫውን መዜረፍ ነው የላሊን ሰው ግጥም ሊርም ብል መነሳት። እያንዲንዲችን ሌዩ ሆነን እንዯተፈጠርነው ሁለ እያንዲንደ ግጥምም ግሊዊ ሌዩና ከገጣሚው አጠቃሊይ ሁነት ጋር ጥብቅ የሆነ ዜምዴና እንዲሇው ሌብ ማሇት ያስፈሌጋሌ። ገጣሚ ሆን ብል ዛማ ቢሰብር ተከምዶዊውን ያገጣጠም ስርዓት ቢጥስ ሃርመኒ ቢያፋሌስ እንኳ እንዯዙያው እንዯእሱነቱ የራሱን አሻራ ይዝ ነው መነበብ መጠናት ሇትውሌዴ መተሊሇፍ ያሇበት። ስሇዙህ በበኩላ ግጥሞቼ የማንም ሰው እጅ እንዱነካቸው አሌፈቅዴም። ከተነበቡ ከታተሙ በኋሊ ግን አንባቢ እንዯመነካቱ መጠን እንዯገባው ቢተረጉማቸው ያ የኔ ጉዲይ አይሆንም።
ታሪኩ፦ በዙህ አካሄዴ እንግዱህ ግጥም መተቸት ማሇት በግጥም ሊይ ኂስ መቅረብ የሇበትም እያሌክ ነው?
ዓሇማየሁ፦ በፍጹም! ኂስ የጥበብ ስራዎችን ከ አንባቢ ከተመሌካች ከተዯራሲ ጋር የሚያገናኝ ቀና መንገዴ ነው። ኂስ ተናጋሪና አዴማጭን የሚያዯማምጥ የሬዱዮ ሞገዴ ነው። ኂስ የጥበብ ሰውን ሇተሻሇ ስራ የሚያነሳሳ የሚኮረኩር የሚያነቃቃ ቅመም ነው። የኂስ ጥበብ በዲበረባቸው አገሮች የጥበብ በረከቶችም አስዯናቂ በሆነ ፍጥነትና ሌእሌና እያዯጉ መሆናቸውን የዓሇም የስነ ጽሑፍ ታሪክ ያስረዲሌ። የግጥም ስራዎች ያሇ ኃያሲ የጽሌመት እንቁዎች ናቸው። ያብረቀርቃለ ዋጋቸው ከፍተኛ ነው ግን አይታዩም ሌሌህ ፈሌጌ ነው። ግጥም የሚፈከር የሚተነተን የሚተረጎም የሚወረስ የጥበብ ዗ርፍ ነው። ታዱያ ግጥምን ከኃያሲ እንዯምን እንሇየዋሇን? ሆኖም ግን አንዴ ተገቢ የሆነና ማንም ሉክዯው የማይችሌ ሃቅ አሇ። ማሽሟጠጥ አሽሙርና አግቦ ከኂስ ተርታ የማይሰሇፉ ምናምንቴዎች ናቸው።
ታሪኩ፦ በግራፊቲ መጽሐፍ መግቢያ ሊይ እስቲ ግጥም ሌጻፍ ተብል ግጥም አይጻፍም! ትሊሇህ ታዱያ እንዳት ነው ግጥሞችህን የምትጽፈው?
ዓሇማየሁ፦ የግጥም ነገር ሇኔ ሁሌ ጊዛ እንግዲ ነው። ግጥም እጽፋሇሁ ብዬ ግጥም መጻፍ አይቻሇኝም። ግጥም አሌጽፍም ብዬም ከመጻፍ አሌታቀብም። ግጥም ስጽፍ አብሮኝ ግጥሙን የሚያምጥና የሚወሌዴ ሰብእና ውስጤ አሇ። ግጥም ስጽፍ ብእሩን ጨብጦ ተመስጦዬን ወርሶ ሌምዴና ባህሊዊ እውቀቴን ገን዗ቡ አዴርጎ ቃሊት የሚያቀብሇኝ ዛማ የሚያወርዴሌኝ ቀሇም የሚገፋሌኝ ሰብእና ውስጤ አሇ። ያ ስውር ሰብእና ግ዗ፍ ካሌነሳ ግጥም አይሆንሌኝም። ሇዙህ ነው እስቲ ዚሬ ግጥም ሌጻፍ ብል መነሳት አዲጋች የሚሆነው። እንዱያውም አንዴ ጊዛ የሥነ ጽሑፍ ስራዎቼን ሇመስራት መዯበኛ ስራዬን አቁሜ በስምንት ወራት ጊዛ ውስጥ አንዱት ግጥም ጠብ እንዲሊሇች አስታውሳሇሁ።
ታሪኩ፦ ላሊው የተሇየና ከዙህ በፊት ያሌተሞከረ ስራህ ሐይኩ ነው። ሐይኩ ብል ግጥም ሇመጻፍ ምን አነሳሳህ እንዳትስ ጀመርከው?
ዓሇማየሁ፦ እንዯነገርኩህ ሇየት ያሇ ነገር መሞከር እወዲሇሁ። ከሐይኩ ጋር የተዋወኩት በንባብ ነው። ሐይኩን ገፍቼ እንዴጽፍ የገፋፋኝና ከአጻጻፍ ጥበቡ፤ ከፍሌስፍናው ጋር ያቀራረበኝ Poets.com የተሰኘ ዓሇም አቀፍ የባሇቅኔዎች ማህበር አባሌ መሆኔ ይመስሇኛሌ። በወቅቱ ሐይኩን በመጻፍና በመተንተን እሳተፍ ነበር። የአጻጻፍ ጥበቡ እየገባኝ ሲመጣም በአማርኛ ሞከርኩትና ያቺ መጽሐፍ BI-LINGUAL ሆና ሇመታተም በቃች።
ታሪኩ፦እስቲ ስሇሐይኩ አጀማመር ምን የምትሇው ነገር አሇህ?
ዓሇማየሁ፦ በመጽሐፌ መግቢያ ሊይ እንዲብራራሁት ሐይኩ ሬንጋ ከተሰኘ የቅኔ መንገዴ ተገንጥል የወጣ እራሱን የቻሇ የቅኔ ቤት ነው። ሬንጋ ሁሇት ወይም ከዙያ በሊይ የሆኑ የቡዲ መነኮሳት/ፈሊስፎች በዯቦ የሚ዗ርፉት ረ዗ም ያሇ የጃፓኖች ቅኔ ነው። ሌብ በሌ ያገራችን ባሇቅኔዎች
ቅኔ ሲ዗ርፉ አንደ የጀመረውን ላሊው ከምሊሱ ነጥቆ እንዯሚሞሊውና እንዯሚጨርሰው አይነት ነገር መሆኑ ነው። ታዱያ ማትሱኦ ባሾ የተሰኘ ባሇቅኔ የሬንጋ መክፈቻ የሆነውን ባሇሦስት ቤት ስንኝ ማሇትም ሖኩ እራሱን የቻሇ ምለእ የሆነ ቅኔ ነው የሚሌ ሃሳብ አመነጨና በርካታ ወጥ ሖኩዎች ጻፈ። ላልች ዯቀመዚሙርት መሌምልም ሖኩን ተወዲጅ የቅኔ ቤት አዯረገው። ከዙያ በኋሊ የመጣ ሺኪ የተሰኘ ላሊ ባሇቅኔ ዯግሞ ሖኩ የሚሇውን ስያሜ ወዯ ሐይኩ ቀየረው።
ታሪኩ፦ አጻጻፉስ፤ ሐይኩን ከላልች ግጥሞች የሚሇየው ምንዴን ነው?
ዓሇማየሁ፦ ሐይኩ ቅሌሌ ያሇ የቅኔ ቤት ነው። እንዱያው በጥቅለ እጅግ በጣም ተሇምዶዊ የሆኑ የንግግር ቃሊትን ነው ሐይኩን ስንጽፍ መጠቀም ያሇብን። የሐይኩ ውበቱ የቃሊቱ ቅሇትና ተራነት ነው። ተራ የሆነውን የተፈጥሮ ትእይንት በተራ ቃሊት ሇማንኛውም አንባቢ መጻፉ ነው የሐይኩ ምጥ። ከዙህም ላሊ ሐይኩ ቁጥብ ነው። እንዯላልቹ የግጥም ዗ሮች ቃሊት አያዜረከርክም ሃሳብ አያንዚዚም። ታዱያ ያ ቅሌሌ ያሇ ቁጥብ ቅኔ ስእሌ መሳሌም ይኖርበታሌ። በተዯራሲው ሌቦና ውስጥ የሚታይ የሚሸተት የሚዯመጥ የሚዲሰስና የሚቀመስ ጉሌህ ስሜት ማስረጽ መቻሌም አሇበት ሐይኩ።
ታሪኩ፦ በመጽሐፍህ መግቢያ ሊይ እንዲሰፈርከው ( ሊንብብሌህና ) በአጠቃሊይ ሐይኩ በተፈጥሮ በመማረክ ተጸንሶ በተቆጠሩ ቀሇማት ተሰዴሮ በቀሊሌ ቋንቋ በምስሌ ከሳች ቃሊት የሚ዗ረፍ ፍሌስፍናዊ ቅኔ ነው ብሇሃሌ። በተሇይ ሐይኩ ፍሌስፍናዊ ቅኔ የተሰኘበትን ምክንያት ብታብራራሌን?
ዓሇማየሁ፦ የዙህ ዗መን እውቀትና የቡዱዜም አስተምህሮ አጠቃሊይ ይ዗ት ቡዱዜም ከሐይማኖት ይሌቅ ፍሌስፍና መኾኑን እንዯሚያመሇክት ሌብ እንበሌና ጨዋታችንን እንቀጥሌ። ሇአብዚኛው ሐይኩ ፍሌስፍናዊነት የባህሪው ነው። ሐይኩ ዏይነ ጉዲዩ ተፈጥሮ በመሆኑ ምክንያት ከቡዱዜም ፍሌስፍናና አስተምህሮ ጋር የጠበቀ ቁርኝት አሇው። ያገራችን የግእዜ ቅኔያት ከመጽሐፍ ቅደስና ከነገረ መሇኮት ጋር የጠበቀ ትስስር እንዲሊቸው አይነት መሆኑ ነው። አንዴ ሐይኩ የቡዱዜምን አስተምህሮ ሇማያውቅ ሰው የአንዴ የተፈጥሮ ቅጽበታዊ ሁነት ቅጂ ቢሆን ያው ሐይኩ የቡዲን ፍሌስፍና ሊዋቀ ሰው ግን ተጨማሪ ትርጓሜ አሇው። ነገሩን ሇማብራራት ሁላ የምጠቅሰውን ካገራችን የግዕዜ ቅኔ አንዴ ጉባኤ ቃና ሌውጣሌ?
ታሪኩ፦ በሚገባ ቀጥሌሌኝ
ዓሇማየሁ፦ ነዲያን ሇኤድም
በነገራችን ሊይ ይህቺን ጉባኤ ቃና ያገኘኋት ከጥቂት ዓመታት በፊት የዜዋይን መንዯሮች በጋሪ ሲያስጎበኘኝ ከነበረ ባሇጋሪ ነው። ባሇጋሪው ጉባኤ ቃናዋ የኔ ሳትሆን የላሊ ባሇቅኔ ናት ብል እንዲጫወተኝም አስታውሳሇሁ። ሌቀጥሌሌህ
ነዲያን ሇኤድም እምንዲቢሆሙ ዴህኑ
ቀይህ መስቀሌ ይረዴኮሙ አኮኑ
የጉባኤ ቃናው ትርጓሜ የዙህ መንዯር ችግረኞች /ዯሃዎች/ ከመከራቸው ዲኑ። ቀይ መስቀሌ የተባሇው ዴርጅት ይረዲቸዋሌና የሚሌ ነው። ታዱያ የመጽሐፍ ቅደስን ታሪክ እማያቅ ሰው ይህን ቅኔ በጥሬው ነው የሚረዲው። ማሇት ችግረኞቹ በቀይ መስቀሌ ዴርጅት መረዲታቸውን ከችግራቸውም መሊቀቃቸውን ነው። ነገር ግን ክርስትናን የሚያቅ ምስጢረ ሥሊሴን ያነበበ ሰው ከሊይ ሊይ ትርጓሜው በተጨማሪ የቅኔውም ምስጢር ይገባዋሌ። የኤዯን ገነት ችግረኞች የሆኑት አዲምና ሔዋን በክርስቶስ ዯም ከሞት እዲ ነጻ መውጣታቸውን ይረዲሌ ማሇት ነው። ሐይኩም እንዱሁ አንባቢውን ይፈሌጋሌ። የሐይኩ ትርጓሜና የመወረስ ኃይሌ እንዲንባቢው የመረዲት የመተርጎምና የመነካት አቅም ይወሰናሌ። ሇዙህም ነው ሐይኩ Deceptively Simple የግጥም አይነት የሚባሇው።
ታሪኩ፦ ሐይኩን ከቡዱዜም ጋር የሚያዚምዯውን ተንተን አዴርገህ ሌታስረዲን ትችሊሇህ?
ዓሇማየሁ፦ ታሪኩ! በሐይኩና በቡዱዜም መካከሌ ያሇውን ዜምዴና ሇማስረዲት ሁሌጊዛም የሚጠቀስ አንዴ ፖፑሊር ጥቅስ አሇ እሱን ሌበሌሌህና ትርጓሜውን እንወያይበት።
ታሪኩ፤ መሌካም ነው ቀጥሌ
ዓሇማየሁ፦ Inaddition to its explicit reference to nature, haiku usually consists some sort of implicit Buddhist reflection on it. In Buddhist metaphysics are three important ideas about natural things that they are transient, that they are contingent and that they suffer
ሐይኩ ማሇት ውዲሴ ተፈጥሮ ወይም ነገረ ተፈጥሮ የሆነ የቅኔ ቤት መሆኑን እያሰብን ውይይታችንን እንቀጥሌ። በቡዱዜም ሜታፊዙክስ ተፈጥሮን በተመሇከተ ሦስት ዓቢይ ቁምነገሮች ይነገራለ። እነሱም ተፈጥሮ ማሇት ወቅቶች ዗መናት ሰዎች አራዊትና እጽዋት በሙለ ጊዛያዊና ኃሊፊ መሆናቸው። እነዙሁ የተፈጥሮ ግሇኛ ወኪልች በስቃይ ዐዯት ውስጥ መመሊሇሳቸውና በተፈጥሮ ውስጥ የሚከናወኑ ሁነቶች በምክንያትና ውጤት ሰንሰሇት የተሰናሰለም ያሌተሰናሰለም መሆናቸው ነው።
ዓሇማየሁ፤ እየተከተሌከኝ ነው?
ታሪኩ፤ በሚገባ ቀጥሌሌኝ
ዓሇማየሁ፤ ሐይኩ የሚጻፈው ስሇተፈጥሮ ነው ብሇናሌ። ታዱያ በሐይኩ ውስጥ የሚወሳ የቅጠሊት መርገፍ፤ ያበቦች መጠውሇግ የወንዝች መጉዯሌ የጸሐይ መጥሇቅ ወ዗ተ ተፈጥሮ በስቃይ ዐዯት ውስጥ መመሊሇሷን ያመሇክታሌ። የወቅቶች መፈራረቅ የ዗መናት ጉዝ የአበቦች መፍካት የጸሐይ መውጣት የኅጻናት መወሇዴ የፍጡራን ተራክቦ ወ዗ተ ዯግሞ ነገሮች በሙለ ጊዛያዊና ኃሊፊ መሆናቸውን እንዱሁም የተፈጥሮ ክስተት ሁለ በምክንያትና ውጤት ሰንሰሇት የተሰናሰሇም
ያሌተሰናሰሇም መሆኑን ያመሇክታሌ ሲለ የሐይኩ ተንታኞች ያስረዲለ። ሇዙህም ነው ሐይኩን ከቡዱዜም ጋር የሚያዚምደት።
ታሪኩ፦ አሁንም ከመጽሐፍህ መግቢያ ሌጥቀስና ሐይኩ ሇመጻፍ የተነሳሳ ሐይካቢም ከተፈጥሮ ጋር መዋዯዴ መፋቀር መተጫጨት በስጋ ወዯሙም መጋባት አሇበት ትሊሇህ፤ ታዱያ አንዴ ሰው ሐይኩን ሇመጻፍ ተፈጥሮን ከመውዯዴ በተጨማሪ የቡዱዜምን ፍሌስፍና ማወቅ አሇበት ማሇት ነው?
ዓሇማየሁ፦ በፍጹም የቡዲን ትምህርት ምንም ሳያውቁ ዴንቅ ሐይኩ መጻፍ ይቻሊሌ። ሇዙህም ነው ሐይኩና ቡዱዜም ባህርያዊ የሆነ ትስስር አሊቸው የሚባሇው።
ታሪኩ፤ ሐይኩን ሇመጻፍ የተነሳ አንዴ ወጣት ኢትዮጵያዊ ቢኖር ምን ትመክረዋሇህ? የአጻጻፍ ጥበቡን ከማን መማር ይችሊሌ?
ዓሇማየሁ፤ ሐይኩን መጻፍ የሚማሩት ትምህርት ቤት በመግባት ወይም ታሊሊቅ መጻህፍትን በማንበብ ወይም የቡዲን አስተምህሮ በመሸምዯዴ አይዯሇም ባሾ እራሱ እንዲሇው Learn of the bamboo from the bamboo and learn of the pine from the pine tree ባሾ ይህን ያሇው ዴንቅ የሐይኩ ጸሐፊ ሇመሆን በየእሇቱ ቸሌ የምንሊቸውን የተፈጥሮ ክስተቶች አትኩረን ብናስተውሊቸውና ብንመራመርባቸው ከነሱ ብቻ ብዘ መማር እንችሊሇን ሉሌ ፈሌጎ ነው። ሐይኩ እዙያው ጉርስ እዙያው ትፍት የሚዯረግ የቅኔ ቤት ነው። ብዘ ማሰሊሰሌና ቃሊት መምረጥ ማጋነን ወይም ማኮሰስ ሃሳቡን ማብሰሌሰሌና መሰሇቅ የሐይኩ ጸሐፊ ስራ አይዯሇም። ጀማሪ ሐይካቢ ላሊው እራሱን ማስተማር ያሇበት አቅሌል መጻፍን መሌመዴ ነው። ቃሊት መቆጠብን በፊዯሌ ስእሌ መሳሌን መሌመዴ ያስፈሌጋሌ። የቡዱዜም ትምህርት ማንም ሉረዲው በሚችሌ ቀሊሌ ቋንቋ ነውና የተጻፈው መሇስ ቀሇስ እያለ እሱን ማንበብም የሚጎዲ ነገር አይሆንም።
ታሪኩ፤ እንዱያው ሐይኩ ቀሊሌ የግጥም ዗ር ነው ተባሇ እንጂ ሇኔ ቀሊሌ ሆኖ አሊገኘሁትም። አንዴ ሰው እንዯአንባቢ ሐይኩ ሲያነብ በቀሊለ ሉረዲው የሚችሇው እንዳት ነው?
ዓሇማየሁ፤ ከራሴም ሌምዴ ከላልች ሰዎች ተሞክሮም እንዯተረዲሁት ሐይኩን አንብቦ ሇመረዲትና ሇማጣጣም ሌምምዴ ይጠይቃሌ። ይህ አይነቱ ሌምምዴ አስፈሊጊ የሆነው ታዱያ ሐይኩ በባህርይው ከብድ ሳይሆን ነገርዬው እንግዲ ጥበብ በመሆኑ ብቻ ነው። ሐይኩ እንዯሇመዴነው መዯበኛ የግጥም አይነት ስሜትና ትርጓሜ የሇውም። የሐይኩ መጽሐፍ የፎቶግራፍ አሌበም ማሇት ነው። በያንዲንዶ ሐይኩ አንባቢ መፈሇግ ያሇበት ምስሌ ነው። ባሇሐይኩው የቀዲውን የተፈጥሮ ትእይንት ማየትና ያቺን ቅኔ በወሇዯበት ቅጽበት የተሰማውን ስሜት ሇማግኘት መታተርና መፈሇግ ነው የሐይኩ አንባቢ ፈንታ።
ታሪኩ፤ ሇዙህ ቃሇምሌሌስ ስ዗ጋጅ ስሇሐይኩ ትንሽ ሇማንበብ ሞክሬ ነበር። ጃፓን ውስጥ ከ዗መናት በፊት የተጀመረው ሐይኩ ዚሬ ሊይ እንዱህ አይነቱን ዓሇም አቀፍ ትኩረት እንዳት ሉያገኝ ቻሇ?
ዓሇማየሁ፦ በአሁኑ ወቅት በእንግሉዜኛና በላልችም የእስያና የአውሮፓ ቋንቋዎች በርካታ የሆኑ ሐይኩዎች በየእሇቱ ይጻፋለ ይታተማለ። የአሜሪካ ኮላጆችና ትምህርት ቤቶች ሐይኩን ሇሌጆቻቸው በሚገባ ያስተምራለ። ሐይኩን ዚሬ ዴረስ ተወዲጅ የግጥም ዗ር ያዯረገው ቀሇሌ ያለ ቃሊት መጠቀሙ ተፈጥሮን ዓይነ ጉዲዩ አዴርጎ መነሳቱ እንዱሁም በጥቂት ስንኞች መቋጨቱ ይመስሇኛሌ። በዙህ ጥዴፊያ በተዋከበ ዓሇም ውስጥ የነ ሼክስፒርን ዎርዴስዎርዜን ብላክን ዊትመንን ፑሽኪንን እጹብ ዴንቅ ቅኔዎች ማን ትእግስት ኖሮት ያነባሌ?
ሐይኩ 42
ግርማ ላሉት
ሙለ ጨረቃ የዯመና አይነርግብ አጥሌቃ
ከዋክብት ሙዴ ያዘባት
ሐይኩ ገፅ 29
ታሪኩ፤ በሐይኩ ሊይ ተጨማሪ ጥያቄ ካሇኝ እመሇስበት ይሆናሌ፤ ከዙያ በፊት ግን አንዴ ጸሐፊ ካገሩ ከወጣ ከባህር እንዯወጣ አሳ ነው የሚባሌ አባባሌ አሇ። ይህ አባባሌ የፈጠራ ችልታውና ዯጋግሞ የመጻፍ ዕዴለ ይመክናሌ ሇማሇት ይመስሇኛሌ። በዙህ ረገዴ አንተ ከጽሁፍ ስራህ የተሇየህ እንዲሌሆንክ የምታሳትማቸው መጽሐፎች ይመሰክራለ ይህ እንዳት ሉሆንሌህ ቻሇ?
ዓሇማየሁ፤ ሇመጻፊያ ጊዛ ወስኜ አሊቅም። አገር ቤት ሳሇሁም የምጽፈው አንዲንዳ ነው አሁንም የምጽፈው አንዲንዳ ነው። የምጽፈው ነገር ከመጣሌኝ የትም ቢሆን ከመጻፍ አሌታቀብም ሇመጻፍ ብዬ የማዯርገው ከመዯበኛው ሩቲን የወጣ ነገር የሇም። የወዯዴኩትን ብቻ አነባሇሁ ሲመጣሌኝም እጽፋሇሁ።
ታሪኩ፤ ስራዎችህን እንዲነበብኳቸው በዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ህይወትና አጠቃሊይ ገጽታ ሊይ ብዘ የጻፍክ አይመስሌም ይህ ሇምን ሆነ ትሊሇህ። ሇወዯፊቱስ ምን ታስባሇህ?
ዓሇማየሁ፤ ካገሬ ከወጣሁ ገና ጥቂት ጊዛ ነው። ቶል ቶል መሇስ እያሌኩም ከምወዲት አገሬ እና ያሇኝን ሁለ ከሰጠኝ ማኅበረሰብ ፍቅር መቀሊወጤ አሌቀረም። ውስጤ አሁንም የሚኖረው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው። የምነካበትና የምኮረኮርበት እሴት እዙያው አገር ቤት ያሇው ነው። ከሆነሌኝ ዯግሜም ሰሌሼም የምጽፈው ስሊገር ቤት ጉዲይ ቢሆን ዯስ ይሇኛሌ። ምናሌባት በውጭ አገር ከቆየሁና ኪናዊ ኩርኮራው ካሇ ግን ስሇዙሁ አገር መጻፍ እችሌ ይሆናሌ።
ታሪኩ፤ ከገጣሚነት በተጨማሪ በጋዛጠኝነት ትታወቃሇህ ጋዛጠኛ መሆን ሇዯራሲነት ምን የሚፈይዯው ነገር አሇ? ይህን ያመጣሁት እንዯ በዓለ ግርማ፤ ብርሃኑ ዗ርይሁን ላልችም ብዘ መጥቀስ ይቻሊሌ ያለት ዯራሲዎች ጋዛጠኛም ነበሩ እስቲ ስሇሁሇቱ የሙያ ዗ርፎች መዯጋገፍ ምን የምትሇው ነገር አሇ?
ዓሇማየሁ፤ ጋዛጠኛ ሁለ ዯራሲ ወይም ገጣሚ መሆን የሚችሌ አይመስሇኝም። ጋዛጠኝነት በስራ ሌምዴና በትምህርት የሚያገኙት በፍሊጎትና በሙከራ የሚያዲብሩት የተከበረ ሙያ ይመስሇኛሌ። ዯራሲነት ግን ከዙህ የተሇየ ነው የዴርሰት ትምህርት የተማረ ሁለ ዯራሲ መሆን የሚችሌ አይመስሇኝም። ዯራሲ ይወሇዲሌ ሌሌህ ፈሌጌ ነው። የሁሇቱን ሙያዎች መዯጋገፍን በተመሇከተ ግን በጋዛጠኝነት ህይወት ማሇፍ ሇዯራሲ ሃሳብን ሇመቆጣጠር ቋንቋን ሇማዲበርና ሇመግራት ተጨማሪ ትምህርት ቤት ይሆናሌ ብዬ አስባሇሁ። በጋዛጠኝነት ዯጃፍ ሳያሌፉ ግን አስዯናቂ የመተረክ ችልታቸውን ያሳዩ ቁጥር ስፍር የላሊቸው ዴንቅ ዯራሲያን በዓሇም ዘሪያ መኖራቸውን ሌብ እያሌን።
ታሪኩ፤ ላሊው ጥያቄዬ ቋንቋን የተመሇከተ ነው። ሇህጻናትም ትጽፋሇህ በወዱህ በኩሌ ዯግሞ ግጥሞችህ አለ። በግጥሞችህ ሊይ የሚታየው የዲበረ የቃሊት አጠቃቀም ሲሆን የኅጻናቱ ዯግሞ ቀሇሌ ብል ነው የተጻፈው። ይህ ከበዴ ያሇ ነገር ይመስሇኛሌ። አንተ እንዳት ሌታስማማው ቻሌክ?
ዓሇማየሁ፤ ሕጻናት ሌጆች መሊእክት ነው የሚመስለኝ። ሌጆች በጣም ይገቡኛሌ። ከሌጆች ጋር በመተያየት ብቻ እናበባሇሁ። የሚያስቡትንና የሚወደትን የፈሇጉትንና ያሌፈሇጉትን ነገር ሇማወቅ አፍታም አይፈጅብኝ። ስሇዙህ ሇነሱ ስጽፍ ትንሽ ሇ዗ብ ትንሽ ጸዲ ትንሽ ፈካ ማሇትን እየተማርኩ ነው። ይህም ሆኖ ግን ጥሩ የህጻናት ዴርሰት ጸሐፊ ነኝ ብዬ አሊስብም። ከህጻናት ገና ብዘ መማር ገና አብሬያቸው መሳቅና ከፍንዯቃቸው ንጽህናን መውረስ ይጠበቅብኛሌ። ዓሇምን በገራገር አይን መመሌከትን ሰዎችን በእኩሌ አይን ማየትን ተፈጥሮን በግሌቧ መረዲትን ከነሱ መማር እፈሌጋሇሁ።
ያሊሇቀ ግራፊቲ
ሳትፈሌጋት ሳታውቀው እጅህ የገባች ሚዲቆ በሄዯችበት ትከተሊታሇህ እንጂ አንተ ወዲሻህ አትመራትም። No matter how hard you may try, you have no control over your own life and your own destiny, like a piece of trunk on a mighty river…
ታሪኩ፤ BETSY AND THE SUPERCOPPTER አዱሱ መጽሐፍህ ነው ማነው ያተመሌህ? የት ነው የታተመው? ታሪኩስ ስሇምንዴን ነው?
ዓሇማየሁ፤ ሰሞኑን የታተመችው የኔዋ አነስተኛ መጽሐፍ ያሳተማት ፐብሉሽ አሜሪካ የተሰኘ ሜሪሊንዴ ያሇ አሳታሚ ነው። ታሪኩም ቤትሲ ስሇምትሰኝ ስሇ አንዱት ጎበዜ ተማሪ ነው። ታሪኩ በጥቂቱ
አዴቬንቸርን ማሳየትን በጥቂቱ ሞራሌን ማስረጽን በጥቂቱ ዯግሞ ቴክኖልጂን ማስተዋወቅን ያካተተ ነገር ይመስሊሌ።
The moment she completed the sentence, the roof of the classroom slid and opened. All the kids and the teacher were surprised to see the roof open and as they were enjoying watching the clear sky, a helicopter appeared and the pilot called for Betsy with a loud speaker.
He said "Dear Betsy, here is my Supercopter, come aboard and I will take you to the place you wish to visit. I will take you to Paris and we will visit the Eiffel Tower."
"What is a Supercopter and who are you?" Betsy asked
"I am Uncle Michael and I am in charge of rewarding kids who are diligent, obedient and nice. I could see you are the only student who started to complete the sentence and I will happily grant you your wish."
Betsy and the Supercopter page 6
ታሪኩ፦ የዓሇማየሁ ሩባያትን ከጻፍክ በኋሊ ያሳተምከው ግራፊቲ ጥቂት የእንግሉዜኛ ግጥሞች አለበት ቀጥል ዯግሞ ሐይኩ ግማሹ እንግሉዜኛ ነው። የሰሞኗ BETSY AND THE SUPERCOPTER ሙለዋን በእንግሉዜኛ ነው የተጻፈችው። ነገሩ እንዳት ነው ማሇቴ የምን ጠጋ ጠጋ ነው?
ዓሇማየሁ፦ አጋጣሚ ነው እንጂ ሆን ተብል የተዯረገ ነገር አይዯሇም። እንግሉዜኛ ሇኔ በትምህርት በንባብና ከተናጋሪዎቹ ጋር አብሮ በመኖር ያገኘሁት ዯባሌ ቋንቋ ነው። እንዲማርኛው እንዲሻኝ የምቦርቅበት ያሇምኩትን የቃዠሁትን የተሰማኝን እና የተነካሁበትን ሁለ የምተነፍስበት ቋንቋ አይዯሇም። ግን አንዲንዴ ሃሳቦች አለ በሃበሻ ቋንቋ እሺ ብሇው የማይወሇደ፤ ቢወሇደም እንኳ ስሜት የማይሰጡና ባእዴ ባእዴ የሚሸቱ። እንዯዙህ አይነቶቹ ሃሳቦች ወዯኔ ከመጡ ብቻ ነው በእንግሉዜኛ የምሞክራቸው።
ታሪኩ፤ በውጭ ያሇው የኢትዮጵያ የሥነጽሑፍ ዯረጃ በአንተ እይታ ምን ይመስሊሌ ያገር ቤቱስ?
ዓሇማየሁ፤ ያገራችን ሥነጽሑፍ በተሇይ ዯግሞ ሥነግጥም እያዯገ መሆኑ ነው የሚሰማኝ። አገራችን ዴንቅ ባሇቅኔዎችን እያፈራች ነው። ክብሩ ይስፋ ሇጥበብ አምሊክ! በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ
የሚታተሙ መጻሕፍት በቁጥርም በጥራትም እያዯጉ መምጣታቸው ዗መኑ የኢትዮጵያ ሥነጽሑፍ እመርታ ያሳየበት መሆኑን የሚያመሇክት ይመስሇኛሌ።
ታሪኩ፤ በስነግጥሞችህ ሊይ ተጽእኖ ያሳዯረብህ ኢትዮጵያዊ ገጣሚ ካሇ ማነው?
ዓሇማየሁ፤ ዴምቅ ብል የሚታይ ተጽእኖ ያሳዯረብኝ ገጣሚ ያሇ አይመስሇኝም። ይህም የሆነው የመርጋትና አንዴን ያጻጻፍ ብሌሃት ሙጥኝ ብል የመያዜ ዜንባላ ስሇላሇኝ ይመስሇኛሌ። ካንደ ያጻጻፍ ብሌሃት ወዯላሊው መዜሇላ ከዙህ ክብር ሳይነሳኝ አሌቀረም። በተረፈ የቀዴሞዎቹ ያገራችን ገጣሚያን በሙለ የግጥም አጻጻፍ ጥበብ መምህሮቼ ናቸው። አሁንም በመጠየቅ በመመርመርና በመፈሇግ ሊይ ነኝና ወጣቶቹ ገጣሚያንም ጭምር የኔ መምህራን ናቸው። ገጣሚዎቻችንን በሙለ በተቻሇኝ መጠን አነባቸዋሇሁ አጠናቸዋሇሁ እማርባቸዋሇሁ።
ታሪኩ፤ ስሇ ቃሇምሌሌሱ እጅግ በጣም አመሰግናሇሁ።
ዓሇማየሁ፤ እግዙአብሔር ያክብርሌኝ ታሪኩ! ግን ሐይኩ ግጥም ኂስና ሕይወት አሁን የተወያየንባቸው ሁለ እና ላሊም ብዘ ብዘ ብዘ ነገር መሆናቸውን እያብሰሇሰሌክ ሌሇይህ?

No comments:

Post a Comment